. እንኳን ደህና መጡ
ተስፋ ሕይወት ሰንበት
ትምህርት ቤት
የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት በ1990 ዓ.ም ተመሰረተ ።
. ተስፋሕይወት
"እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ" ማቴ 28÷20
በ1991ዓ.ም አባ ፍስሀ ተ/ጽዮንን በመያዝ ቤት ለቤት በመዞርከ ምዕመናኑ በተሰበሰበው ገንዘብ 20 የወጣቶች እና 10 የህፃናት ልብሰ ስብሐት በማሰፋት ለአገልግሎት አብቅተዋል ።
ተስፋ ሕይወት
ከ 1990 ዓ.ም
ጀምሮ
ሰ/ት/ቤት ማለት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወጣቶች እና ህፃናት ስለ ሃይማኖታቸው ስርአት ፣ ዶግማ ፣ ትውፊት እና ታሪክ የሚማሩበት እና እራሳቸውን በመንፈሳዊ ህይወት የሚያንፁበት አና መልካም ፍሬን የሚያፈሩበት ተቋም ነው።
የስም ስያሜ
የሰንበት ትምህርት ቤቱ ስያሜ
የወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ተስፋ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት እየተባለ የሚጠራ ሲሆን ይህ የወ/ጤ/ደ/ብ/ቅ/ገ/ቤ/ክ ተስፋ ህይወት ሰ/ት/ቤት ስያሜው የፀደቀው በ2011ዓ.ም በደብሩ አስተዳዳሪ በመጋቤሐዲስ አባ ኤልያስ(ቆሞስ) ነው ፡፡ ይኸውም ሰ/ት/ቤቱ ለቤተክርስትያኑ ተስፋ መሆኑን ለማመልከት ነው ፡፡
ስለ ሰንበት ት/ቤቱ መሰረታዊ መረጃዎች
ሰንበት ትምህርት ቤቱ 2022 ዓ.ም በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በትምህርት አሰጣጥ እና በአባላት ስነ ምግባር በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ሰንበት ትምህርት ቤት ሆኖ ማየት ።
- በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ህፃናት ትክክለኛውን ትምህርተ ሃይማኖት እና የአብነት ትምህርትን በማስተማር የቤተክርስትያኗን ዶግማ ፣ትውፊት ፣ ቀኖና ፣ ስርአት እና ታሪክ እንዲያውቁ ማድረግ፡፡
- የሰ/ት/ቤቱ አባላት በመናፍቃን እንዳይነጠቁ አስፈላጊውን እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ፡፡
- የተለያዩ መንፈሳዊ ጉባዬዎችን በማዘጋጀት ለምዕመኑ ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር ፡፡
- በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በሚደረጉ ልዩ ልዩ መርሀ ግብራት ላይ በመሳተፍ የቤተክርስቲያኑን አገልግሎት ማገዝ ፡፡
- አባላቱ በሰ/ት/ቤቱ ውስጥ ባሉ ክፍላት ላይ በመሳተፍ መክሊታቸውን እንዲያተርፉበት ማድረግ፡፡
- ሕፃናት እና ወጣቶችን የቤተክርስትያንን ሚስጥራትን በማስተማር የሚስጢር ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል።
- መንፈሳዊ ወጣቶች እና ህፃናት የቤተክርስትያንን እና የሀገርን ታሪክ በሚገባ አውቀው በነገረ
መለኮት ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ተምረው የነገዋን ቤተክትስትያን እና ሀገርን በሃላፊነት ለመረከብ
ብቁዎች ማድረግ ፡፡
- ከስብከተ ወንጌል ፣ ከካህናት እና ከተለያዩ አባላት ጋር ተባብሮ በመስራት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ
ሃይማኖት ፣ ስርአት እና ትውፊት ሳይበረዝ እና ሳይለወጥ ከተውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ
ማድረግ ፡፡
- የሰ/ት/ቤቱ አባላት ያላቸውን መክሊት (ፀጋ) ተጠቅመው ቤተክርስትያንን እንዲያገለግሉ ማድረግ
- ወጣቶች እና ህፃናት የሃይማኖታቸውን ስርአት ፣ ትውፊት እና ዶግማ እንዲያውቁ ፤በስነምግባራቸውም የታነጹ እና ክርስትያናዊ ግብረገብ የተላበሱ እንዲሆኑ ማድረግ ፡፡
- ሃይማኖታቸውን አፅንተው እንዲይዙና እንዲጠብቁ ማድረግ ፡፡ 2ኛ ጢሞ 4፥7-8 "ሃይማኖቴን
ጠብቄአለሁ ወደ ፊት የፅድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል "






